‹‹ አውሬነት Vs ሰብዓዊነት ››

(መላኩ አላምረው)

ሁሉም የምድር ቁሳቁስ (ራሷን ምድርንም ጨምሮ) ለሰው ልጅ ተፈጠሩ እንጅ ሰው ለቁስ አልተፈጠረም፤ ለቁስም አይኖርም፡፡ በምድር ላይ ከሰው ልጅና ከሕይወቱ በላይ ክብር ልንሰጠውም ሆነ ጥበቃ ልናደርግለት የሚገባ ምንም ነገር መኖር የለበትም፡፡ በተለይም የሰውን ልጅ ክቡር ሕይወት ከቁሳቁስ ጋር ማነጻጸር… በተለይም ከሰው ልጅ ይልቅ ለቁስ ማድላት… ይህ የመጨረሻው የውርደት ጥግ ነው፡፡ ይህ በራስ ፈቃድ ከሰውነት ተራ ወጥቶ አውሬነትን መቀላቀል ነው፡፡ (፡›አውሬ ሆዱን የሚሞላለትን የሚበላ ነገር እስካገኘ ድረስ ስለ ነፍስ መጥፋት ጉዳዩ አይደለም፡፡ ያገኘውን ሁሉ እያረደ እየበላ ሕይወቱን ማስረዘም ላይ ብቻ ያተኩራል፡፡ የእርሱን ነፍስ ለማቆየት ሲል የሌላውን ነፍስ ያጠፋል፡፡ አውሬ የሌላው ነፍስ እንደርሱ ነፍስ ብቸኛ የመኖር ዋትና መሆኗን ይረሳል፡፡ በቃ ! ከራበው ማረድ ነው፡፡ እንዲያውም የሌሎችን ነፍስ በማጥፋት ደም ካላፈሰሰ የበላሁ አይመስለውም፡፡ ባጭሩ አውሬ የራሱን ነፍስ ለማኖር የሌላውን ነፍስ ያለ ርህራሄ የሚያጠፋ የምድራችን አረመኔና ጸረ-ሕይወት ፍጡር ነው፡፡)
የሰው ልጅ ግን እጅግ የሚያስተውል አዕምሮ የተሰጠውና ለፍጡራን ሁሉ የሚራራ ክር ፍጥረት ነው፡፡ በተለይም ለመሰሉ ለሰው ልጅ ሕይወት መኖር ዋጋ ይከፍላል፡፡ (ከአውሬዎች ለመጠበቅም አዕምሮውን ይጠቀማል፤ አንዱ ለአንዱ ጋሻ ይሆናል፡፡) ነገር ግን… ሰው በባሕርይው ተለዋዋጭ ፀባያት አሉትና… ሲያድለው ወደ መልአካዊነት ይለወጥና ሁሉንም እኩል ያፈቅራል፡፡ ለሁሉም እኩል ይራራል፡፡ ሳያድለው ወደ እንስሳዊነት ይወርድና ለሆዱ ብቻ የሚኖር ይሆናል፡፡ ከሰው ልጆች ይልቅ ሆዱን የሚሞሉ ቁሳቁሶችን አስበልጦ መውደድ ይጀምራል፡፡ በጣም ሲከፋም ወደ አውሬነት ተቀይሮ የገዛ ወንድም እህቶቹን አሳዳጅ ይሆናል፡፡ በራበው ሰዓት ያገኘውን ሁሉ ማረድ ይጀምራል፡፡ በዚህ ሰዓት የሰዎችን ምክር አይሰማም (አውሬ ሆኗላ)፡፡ እንስሶችንም ሆዱን ለመሙላት ብቻ ነው የሚፈልጋቸው፡፡ የእርሱ ሕብረት አብረውት ከሚገድሉ ጋር ብቻ ይሆናል፡፡
የሚያሳዝነው ደግሞ ወደ አውሬነት የተለወጠ ሰው ይህን ሁሉ ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ሲያከናውን አለማስተዋሉ ነው፡፡ የማስተዋል ጸጋውን ከሰውነት ወደ እንስሳነት በተቀየረ ጊዜ አጥቶታልና የሚያደርገው ነገር ሁሉ ልክ ይመስለዋል፡፡ መግደል የመኖር አንዱ መንገድ እንጅ ነውረኛ የአውሬ ፀባይ መሆኑ ፈጽሞ አይታየውም፡፡ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ወደ አውሬነት ፀባይ የገባን ሁሉ ቆም ብለን እናስብ፡፡ እየተናገርሁ ያለሁት ነገር ተረት ተረት አይደለም፡፡ የሰው ልጅ የሕይወት ሐቂቃ እንጅ፡፡ ከአውሬነታችን ካልተመለስን በቀር ሰብዓዊነትን ልንላበስ አንችልም፡፡ ሰብዓዊነትን ካልተላበስን ደግሞ ከሰዎች ጋር በሰዋ አኗኗር ለመኖር እንቸገራለን፡፡ የሰው ልጅ ብቸኛው የመሸናነፊያ መሳሪያ ‹‹ፍቅርና›› ነው፡፡ ፍቅር ካለ ይቅርታ አለ፡፡ ‹ፍቅርና ይቅርታ ደግሞ በአውሬ ልብ ውስጥ አያድሩም›፡፡
ለገንዘብና ገንዘብ ለሚገዛቸው ቁሳቁሶች ሲባል የሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት መረገጥ የለበትም፡፡ በተለይም በሕይወት የመኖር መብቱን ከፈጠረው ከአምላኩ በቀር ማንም ሊወስንለት አይገባም፡፡ አይደለም የሰው ልጅ ሕይወት የማንኛውም ሕይወት ያለው ፍጡር ነፍስ ከፈጣሪ የተሰጠች ምትክ የሌላት ውድ ሀብትና የመኖር ምስጢር ናት፡፡ ይህች የሕልውና መሠረት በፍጡራን ቁጥጥር ስር የምትሆንበት ተፈጠሯዊም ሆነ ሌላ ምንም ምክንያት የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ “ሰዎች” የሰዎችን ሕይወት የመስጠትም የማጥፋም መብቱ የላቸውም፡፡ ይህ አውሬነት ነው፡፡

ጎህ መጽሄት ሰኔ 2009 ዓ.ም 3ኛ አመት 15ኛ እትም ለንባብ ቀርባለች

ጎህ መጽሄት ሰኔ  2009 ዓ.ም 3ኛ አመት ቁጥር 15.png

ጎህ መጽሄት በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በየ 3 ወሩ የምትታተም መጽሄት ናት::  ጎህ መጽሄት ሰኔ  2009 ዓ.ም 3ኛ አመት ቁጥር 15 ለንባብ ቀርባለች:: ሙሉውን ንባብ  PDF ፋይሉን በመጫን እንድታነቡት በአክብሮት ተጋብዛችሁዋል::

PDF ጎህ መጽሄት ሰኔ 2009 ዓ.ም 3ኛ አመት 15ኛ እትም

 

 

የአዲስ አበባ ከተማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የሚጥስ አዋጅ አጥብቀን እንቃወማለን! (የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ)

ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ

ህወሀት/ኢህአዴግ በ100 ፐርሰንት አሸንፊያለሁ ብሎ ባወጀ ማግስት በመላ ሀገራችን በሁሉም አቅጣጫ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የነፃነት፣ የእኩልነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን በማንገብ የኢትዮጵያ ህዝብ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው፡፡አገዛዙ ይህንን መሰረታዊ የለውጥ ጥያቄ ለማዳፈን ሲል ለማመን በሚከብድ ሁኔታ አስተዳድረዋለሁ በሚለው ህዝብ ላይ ግድያ፣ የጅምላ እስር እና ማፈናቀል ዋነኛ ተግባሩ አድርጎታል፡፡ በዚህ የአገዛዙ ኢ-ሰብዓዊ እርምጃም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ የለውጥ ጥያቄ ማስቆም ባለመቻሉ በድንጋጤና ባልታሰበበት ሁኔታ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመከፋፈል እና በጥርጣሬ እንዲተያይ ለማድረግ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡Semayawi party to welcome Andinet members

ይህ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተረቀቀ የተባለው አዋጅ በጥድፊያ የወጣ፣ግልፅነት የጎደለው፣ህገ መንግስቱን የጣሰ፣በመረጃና በጥናት ላይ ያልተመረኮዘ፣አጠቃላይ የዴሞክሰራሲ መርሆና ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 አላማ ጋር በእጅጉ የተቃረነና ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት አገዛዙ የተነሳበትን የፖለቲካ ትኩሳት ለማብረድ በማሰብ የተቀነባበረ ግልብ ሴራ ነው፡፡

አገዛዙ በተቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን እንደተገለፀው በዚህ አዋጅ የማርቀቅ ሂደት ላይ የተሳተፉት አካለት የኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ኦህዴድ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እንደሆኑ ተገልፅዋል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ አዲስ አበባን ከሚያስተዳድሩትም ሆነ በፌደራል ፓርላማ 100 ፐርሰንት አሸንፊያለሁ ያለው ኢህአዴግና አጋሮቹ ውስጥ እንደ ድርጅት ኦህዴድ ብቻ መሳተፉና ሌሎች ማለትም ብአዴን፣ደህዴንና ህወሃት እንዳይሳተፉ መደረጋቸው በድርጅቱም ውስጥ ታስቦበትና ሙሉ ስምምነት ተደርሶበት የተዘጋጀ ረቂቅ አለመሆኑን እና ተራ የፖለቲካ ሸቀጥ መሆኑን ግልፅ ማሳያ ነው፡፡በዚሁ መግለጫ ላይ አንደተገለፀው በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መስፋፋት ለተፈናቀሉና ወደፊትም ለሚፈናቀሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈለው ለኦሮሞ ብሄር ተወላጅ አርሶ አደሮች እንደሆነ ተገልጧል፡፡ይህም ማለት በዚህ አዋጅ መሰረት በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መስፋፋት ምክንያት ለሚፈናቀሉ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ካሳ የማግኘት መብት የላቸውም ማለት ነው፡፡ ይህ አገላለፅ የዜጎችን ተዘዋውሮ የመስራትና ሀብት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብት የሚነጥቅ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተቀባይነት የለውም፡፡

የህገ መንግስቱ አንቀፅ 49/5 ዓላማ የአገልግሎት አቅርቦትን፣የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምናን እና የጋራ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን አፈፃፀም የተመለከተ ሲሆን ይህ ተረቀቀ የተባለው አዋጅ ግን ከዚህ አንቀፅ በተቃራኒው ተለጥጦ የአዲስ አበባን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት በመንጠቅ ኦሮሞነትን በላዩ ላይ በመጫንና ተገዶ እንዲቀበል በማድረግ ኦሮሞ ያልሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ በገዛ ሀገሩ ባይታወርነት እና እንግድነት እንዲሰማው የሚያደርግ ጨቋኝ አዋጅ ነው፡፡

በዚህ ተረቀቀ በተባለው አዋጅ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሰራተኞች ተመዝግበው ቤት የማግኘት መብት እንዲከበርላቸው ይደነግጋል፡፡ በመሰረቱ የኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት ዋና ከተማ አዳማ መሆኗን በ1994 ዓ.ም የተሸሻለው የክልሉ ህገ መንግስት አንቀፅ 6 ይደነግጋል፡፡ይህ ሆኖ እያለ ህወሃት/ ኢህአዴግ በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ አዲስ አበባ ከተማ ላይ በደረሰበት አስደንጋጭ ሽንፈት ምክንያት የወቅቱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ በምርጫው ማግስት የኦሮሚያ ክልልን ህገ መንግስት በመጣስ በፖለቲካ ውሳኔ የአዳማ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማነት መብትን በመንጠቅና ወደ ህዝብ የመቅረብ መሰረታዊ የፌደራሊዝም ፅንሰ ሃሳብ በመጣስ ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወር አድርገዋል፡፡ይህ ውሳኔ የክልሉን ህገ መንግስት ያላከበረ ስለሆነ ሊፀድቅም ሊፈፀምም አይገባም፡፡

በፌደራሉ ህገ መንግስት መሰረት 9 ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እንዳሉ ሲታወቅ አዲስ አበባ በዚህ ህገ መንግስት በአንቀፅ 49/2 መሰረት ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብትና የራሱን የስራ ቋንቋ የመወሰን መብቱ የአዲስ አበባ ህዝብ እና የሚወክላቸው አካላት ብቻ መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ይህንን ህገ መንግስታዊ መብት በመጣስ የአዲስ አበባ አስተዳድርን የስራ ቋንቋ የሚወስን አዋጅ በፌደራል መንግስት ማውጣት በራሱ በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 9 መሰረት ተቀባይነት የለውም፡፡ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኦሮሞኛን የስራ ቋንቋ ማድረግ አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከስራ እድል በማግለል ኦሮሞ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ቅድሚያ ለመስጠት በማስመሰል በዜጎች መካከል አላስፈላጊ የጥቅም ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርግና በህዝብ መካከል ያለውን መስተጋብር የሚንድ መርዘኛ አዋጅ በመሆኑ በፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡

ከላይ በገለፅናቸው ማሳያ ነጥቦች መሰረት ይህ ተረቀቀ የተባለው አዋጅ የህግም ሆነ የሞራል መሰረት የሌለው ስለሆነ በአስቸኳይ አንዲቆምና የኦሮሚያ ክልል መንግስትም የአዳማን የክልል ርዕሰ ከተማነት ህገ መንግስታዊ መብትን በማክበር አሰተዳደሩን ወደ አዳማ እንዲያዛውርና የአዳማ ከተማ በክልሉ ህገ መንግስት የተሰጠውን የክልል ከተማነት መብት ተከብሮ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚገኙ የኢኮኖሚ፣የፖለቲካ እና የማህበራዊ እድገት ተፈፃሚ እንዲሆን በአፅንዖት እንጠይቃለን፡፡በመጨረሻም ረቂቅ አዋጁ ህወሀት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያን መሰረታዊ የህዝብ ጥያዌ ለመመለስ አቅምም ሆነ ፍላጎት እንደሌለው በግልፅ የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር ለስልጣኔ ይጠቅመኛል ያለውን ሁሉ በህዝብ ላይ ከመፈም ወደኋል እንደማይል ከድርጊቱ ተገንዝበናል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የአዲስ አበባ ህዝብ ይህንን ተረቀቀ የተባለውን ከፋፋይና መርዘኛ ረቂቅ አዋጅ ውድቅ እንዲሆን ጥቃቅን ልዩነቶችን በማሶገድ መሰረታዊ ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት፣እኩልነትና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር አውን መሆን ላይ በማተኮር በአንድነት ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ሰኔ 25 ቀን 2009 ዓ.ም

የኢህአግዘ /EPPFG/ የ ሶስት ወሩን መደበኛ ስብሰባ አካሄደ

 

Reported by Alemayehu Kidanewold

Photo by Michael Mekonnen

በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ July 1, 2017 ዓ ም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ /EPPF Guard/ የ ሶስት ወሩን መደበኛ ስብሰባ አካሄደ:: በአቶ ልዑል ቀስቅስ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው ስብሰባ በጣም በርካታ ህዝብ የተገኘበት እና በዙ የመወያያ ሃሳቦች የተስተናገዱበት ስብሰባ ሆንዋል::

አቶ ልዑል ለተሰብሳቢዎቹ ስለ ውቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ ማለትም የወያኔ ወሮበላ ቡድን በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ላይ እየሰራ ያለውን በዘር እና በጎሳ ከፋፍሎ የመግዛት እና የራሱን የስልጣን ዘመን ለማርዘም እየተጠቀመበት ያለውን እርስ በእርስ የማጋጨት ስራ በመቃወም እንዲሁም በቅርቡ የኦሮሞን እና የአማራ ህዝቦችን እንቅስቃሴ ለማዳከምና ለማከሸፍ በአዲስ አበባ ላይ ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም በማስመሰል እየሰራ ያለውን ድራማ ማንም ሰው የሚረዳውና ለኦሮሞ የመብት ጥያቄ አንዳችም መልስ የማይሰጥ እንደሆነ በአጽንኦት ተናገረዋል ::

በስብሰባው ላይ ከተነሱትም አስተያየቶች መካከል የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር የዴሞክራሲ ፣ የፍትህ ፣ የነጻነት ፣ ህብረተሰቡ በሰላም ያለ ስጋት ሰራተኛው ሰርቶ ፣ ነጋዴው ነግዶ ፣ ገበሬው አርሶ ፣ ተማሪው ተምሮ ለፍቶ ወዘተ…… እሚኖርባትን ኢትዮጵያ ለመፍጠር እና እኩል ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር ፣ የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እና ሌሎችም መሰረታዊ ጉዳዮች እያሉ ፥ ወያኔ በባለፈ ታሪክ በማይረባ የፖለቲካ ቁማር ለሃገር መበታተን ቅንጣት ታክል ሳያስቡ በሃይማኖት ፣ በዘር እና በጎሳ በመከፋፈል በመግደል ፣ መማሰር እና አብዛኛውንም ለስደት በመዳረግ ላይ ስለሆነ ይህንን ዘረኛና ከፋፋይ ቡድን በአንድነት ሆነን ልንታገለው እንደሚገባ ተወያይተዋል ::

ሃገር ልትቀየር የምትችለው በንጹህ የሃገር ፍቅር ፣ በእውቀት ፣ በስራ እንዲሁም እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደፊት በመራመድ ሲሆን የወያኔ ስርአት ግን ለህዝቡ የማይጠፋ እሳትን በማቀጣጠል እርስ በእርሱ እንዲባላን እንዲጨራረስ ለማድረግ እንዲሁም ያለፈን የሃሰት ታሪክ በማጣቀስ ህዝቡ በግድ በዛሬው ታሪክ ሳይሆን በአለፈ የውሸት የፈጠራ ታሪክ እርስ በእርስ በማናከስ እየኖረ እንደሆነ ሁሉም ሰው ሊረዳው እንደሚገባ እና ትናንት ታልቅ የነበርችውን ሃገራችንን ከገባችበት ትልቅ የመከራ አዘቅት ውስጥ ማንም ሳይሆን እራሳችን አውጥተን ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ በስፋት ተነስቶዋል::

image-0-02-05-d54cc442eb5e77843d4c7bfe7306adb6fa162435078cc2198dacd7530d918702-V

 

 

ይህንንም ለማድረግ ሁሉም ተሰብሳቢ በመቆም እና እጅ ለእጅ በመያያዝ በባለፈው ታሪክ ይቅር በመባባል በሃይማኖት ፣ በዘር እና በጎሳ መከፋፈልሉን ወደሁዋላ በመተው ለውደፊቱ በጽናት እና በአንድነት ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍን ታሪክ ለመስራት ኢትዮጵያ ሃገራችንን ዳግም ከፍ ለማድረግ ቃል በመግባት ስብሰባው ተጠናቆዋል ::

ከጨቋኝ መንግስት በፊት ጭቆናን የተቀበለ ሕዝብ መቀየር አለበት (ክፍል-1)

 

እርግጥ በነፃነት መኖር የማይፈልግ ሰው ያለ አይመስለኝም። ይሁን እንጂ፣ “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” እንዲሉ ነፃነት’ም ካላወቁት አይናፍቅም። ነፃነትን የማያውቅ ሰው የነፃነትን ትርጉምና ፋይዳ አይረዳም። የራሱን ነፃነት አያስከብርም፣ የሌሎችን ነፃነት አያከብርም።ስለ ነፃነት ሙሉዕ ግንዛቤ የሌለው ሰው የሕይወትን ትርጉምና ፋይዳ እንኳን መገንዘብ አይችልም።

በመሰረቱ ነፃነት የሕይወት ትርጉም እና ፋይዳ ነው። የሰው-ልጅ ለሕይወት ያለው ስሜት አንፃራዊ ነፃነቱን ለማሳደግ በሚያደርገው ጥረት የሚገለፀው ባለው አንፃራዊ ነፃነት ነው። ሀብት እና ድህነት፤ መፈለግ እና አለመፈለግ፤ ሃይል እና ተገዢነት፤ ጤና እና በሽታ፤ ባህል እና አላዋቂነት፤ ሥራ እና ምቾት፤ ጥጋብ እና ረሃብ፤ መልካም እና መጥፎ፣ ሁሉም አንፃራዊ የነፃነት ማነስ እና መብዛት ውጤቶች ናቸው።

የአማርኛ መዝገበ ቃላት “ነፃነት” የሚለውን ቃል፤ “1ኛ፡- ሌላውን ሳይነኩ የፈለጉትን ነገር የመስራት፥ የመናገር፥ የመፃፍ፣ … መብት። 2ኛ፡- በባዕድ መንግስት ወይም በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር አለመሆን። 3ኛ፡- ራስን በራስ የማስተዳደር፥ የመምራት ስልጣን፥ መብት” እንደሆነ ይጠቅሳል። ሰው (person) ማለት ደግሞ በሃሳብ ወይም በተግባር ራሱን ወይም የሌሎች ሃሳብና ተግባር ወክሎ የሚንቀሳቀስ ነው። በራስ ወይም በሌሎች ሰዎች ፍላጎት መሰረት እየሰሩ፥ እየተናገሩ፥ እየፃፉ፣… በራስ ወይም በሌሎች ፍቃድ እየተንቀሳቀሱ እና ራስን-በራስ እያስተዳደሩ ወይም በሌሎች እየተመሩ መኖር ደግሞ “ሕይወት” ይባላል።

በዚህ መሰረት፣ ሕይወት ማለት እንደ ራስ ፍላጎትና ፍቃድ ወይም በሌሎች ፍላጎትና ፍቃድ መሰረት የሚተውኑባት ቤተ-ተውኔት ወይም ቲያትር (theatre) ናት! በሕይወት ውስጥ እያንዳንዱ ግለሰብ ተዋናይ (Actor) ነው። በእንግሊዘኛ “person” የሚለው ቃል ሥርዖ ቃሉ “persona” የሚለው የላቲን ቃል ሲሆን በመድረክ ላይ ያለ ሰው ውጫዊ ገፅታ ወይም መልክ “outward appearance of a man, counterfeited on the stage” የሚል ፍቺ አለው። ስለዚህ፣ ሰው (person) በሕይወት ትያቲር ላይ የራሱን ወይም የሌላን ሰው ገፀ-ባህሪ በመወከል የሚተውን (personate) ነው።

ሰው የተፈጥሮ (Natural Person) እና ሰው-ሰራሽ (Artificial person) በሚል ለሁለት ይከፈላል። የተፈጥሮ ሰው በራሱ የተውኔቱ ደራሲ (author) እና ተዋናይ (actor) ሊሆን ይችላል። “ሰው-ሰራሽ” ሰው ግን የተፈጥሮ ሰዎች ገፀ-ባህሪን በመወከል የሚተውን ተዋናይ (actor) ነው። “Thomas Hobbes” የተፈጥሮ እና ሰው-ሰራሽ ሰዎች በሕይወት ቲያትር ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡-

“Of persons artificial, some have their words and actions owned by those whom they represent. And then the person is the actor, and he that owneth his words and actions is the author, in which case the actor acteth by authority. So that by authority is always understood a right of doing any act; and done by authority, done by commission or license from him whose right it is.” Leviathan – Thomas Hobbes, Page 84

ከላይ በተጠቀሰው መሰረት፣ “authority” የሚለው ቃል ሥርዖ-ቃሉ “author” የሚለው ቃል ነው። ስለዚህ፣ በአማርኛ “ስልጣን” (authority) ማለት አንድን ነገር ለማድረግ፣ ለመስራት፣ ወይም ለማሰራት የሚያስችል መብት ነው። “ባለስልጣን” ማለት ደግሞ፤ “አንድን ነገር ለማድረግ፥ ለመስራት፥ ወይም ለማሰራት ኣመራርን ለመስጠት፥ ለመወሰን የሚያስችል መብት ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት” ማለት ነው። በአጠቃላይ፣ “ስልጣን” ማለት በተፈጥሮ ወይም በውክልና የተሰጠና አንድን ነገር ለማድረግ፣ ለመስራት፣ ወይም ለማሰራት የሚያስችል “መብት” (right) ነው።

የመንግስት ስልጣን ከእያንዳንዱና ከሁሉም ዜጎች በውክልና የተሰጠ ሀገሪቷንና ሕዝቡን ለመምራት የሚያስችል መብት (authority) ነው። እንደ “Thomas Hobbes” አገላለፅ፣ “መንግስት” ማለት እያንዳንዱ ዜጋ ከሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ጋር በመስማማት፤ “1ኛ፡- የሌላውን መብት ሳይነካ የፈለገውን ነገር እየሰራ፣ እየተናገረና እየፃፈ በሰላም በሀገሩ እንዲኖር፣ እና 2ኛ፡- በባዕድ ሀገር መንግስት ወይም በሌላ ሰው በኃይል ተገዢ እንዳይሆን ጥበቃና ከለላ እንዲያደርግለት፣ 3ኛ ላይ የተጠቀሰውን “ራስን በራስ የማስተዳደር፥ የመምራት ስልጣን፥ መብት”ን በውክልና ለተወሰኑ ሰዎች በመስጠት የፈጠረው አካል ነው።

በመጨረሻም ወደ ፅኁፉ ዋና ነጥብ ስንመለስ፣ በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት በተለይ ባለፉት አስር አመታት የባሰ ጨቋኝና አምባገነን እየሆነ መምጣቱ እርግጥ ነው። በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የነፃነት፥ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በኃይል ታፍኗል። በመሆኑም፣ ይህን ጨቋኝና አምባገነን መንግስት ከስልጣን በማስወገድ የዜጎች ነፃነትና እኩልነት የተከበረበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መዘርጋት አለበት የሚል አመለካከት በሰፊው ይንፀባረቃል። ነገር ግን፣ የኢህአዴግ መንግስት ሆነ ሌላ ማንኛውም መንግስት ከእያንዳንዱና ከሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ከተሰጠው ፍቃድና ውክልና ውጪ ምንም ነገር የማድረግ ስልጣን የለውም።

በመሰረቱ፣ የኢህአዴግ መንግስት በሕዝብ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ የሆነ ተግባር መፈፀም አይችልም። ሕገ-መንግስት ደግሞ በሀገሪቱ ሕዝብና በመንግስት መካከል የተፈረመ የውል ሰነድ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ሰው (person) እንደመሆኑ መጠን በራሱ ፍላጎት መሰረት እየሰራ፥ እየተናገረና እየፃፈ እና በራሱ ፍቃድ እየተንቀሳቀሰ ለመኖር እንዲችል ራሱን በራሱ የማስተዳደር፥ የመምራት መብትና ስልጣኑን ለመንግስት አሳልፎ ሰጥቷል። የኢህአዴግ መንግስት እንዲያስከብር የተሰጠውን ስልጣን የዜጎችን በነፃነት የመስራት፣ የመናገር፣ የመፃፍና የመንቀሳቀስ መብት ለመገደብ አውሎታል። የኢህአዴግ መንግስት ላለፉት አስር አመታት በሕገ-መንግስቱ መሰረት ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት ውጪ ሲንቀሳቀስ ውክልና የሰጠው የኢትዮጲያ ሕዝብ ምን ዓይነት እርምጃ ወሰደ?

በእርግጥ የኢህአዴግ መንግስት እንደ መንግስት በእያንዳንዱና በሁሉም ዜጎች ተፅፎ የተሰጠውን ቲያትር ከመተወን ባለፈ አዲስ ተውኔት የመፃፍና የመተውን ስልጣን የለውም። ነገር ግን፣ ለምሳሌ፣ የፀረ-ሽብር ሕጉን ሲያፀድቅና በዚህም በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ለእስር፣ ለስቃይና ለስደት ሲዳርግ የኢትዮጲያ ህዝብ “በውል ከተሰጠህ ስልጣንና ኃላፊነት ውጪ አዋጅና መመሪያ አውጥተሃል” በሚል ውክልናውን አነሳ? በውሉ መሰረት ለመንግስት የሚከፍለውን ግብር አቋረጠ? ጥቂቶች ሺህዎች ለሞት፥ እስርና ስደት ሲዳረጉ ብዙ ሚሊዮን የሚሆነው የኢትዮጲያ ሕዝብ መብትና ነፃነቱን ለማስከበር ምን ያህል እርምጃ ተራመደ።

ብዙሃኑ የሕብረተሰብ ክፍል መብትና ነፃነቱን አውቆ በራሱና ለራሱ ማስከበር እስካልቻለ ድረስ የኢህአዴግ መንግስት ተቀየረ፥ አልተቀየረ ምን ፋይዳ አለው? የደርግ ሆነ የኢህአዴግ መንግስት መብትና ነፃነቱን ከማረጋገጥ ይልቅ በደልና ጭቆና ሲፈፅሙበት አሜን ብሎ የተቀበለ ማህብረሰብ ሌላ መንግስት ቢመጣ-ባይመጣ ምን ለውጥ አለው? ትላንትና ዛሬ መብትና ነፃነቱን መብትና ነፃነቱን በራሱ ማስከበር የተሳነው ማህብረሰብ የኢህአዴግ መንግስት ከስልጣን ቢወገድ-ባይወገድ ምን የተለየ ነገር ይኖራል። መብትና ነፃነቱን እንዲከበር ሆነ እንዳይከበር ያደረገው መንግስት ሳይሆን ዋናው የስልጣን ባለቤት “ሕዝብ” ነው። ጨቋኝ ስርዓት ባለበት ሀገር ጭቆናን አምኖ የተቀበለ ማህብረሰብ አለ። በእርግጥ “ጨቋኝ” መባል ያለበት ጭቆናን ፈቅዶ የተቀበለ ነው። ሰጪ በሌለበት ተቀባይ አይኖርም። ስለዚህ፣ ጨቋኝ ህዝብ እንጂ ጨቋኝ መንግስት ብሎ ነገር የለም።

በአጠቃላይ፣ መንግስት ሕዝብ እንደፈቀደለት ነው የሚሆነው። ለመብቱና ነፃነቱ የሚከራከር ጠያቂ ማህብረሰብ ባለበት መንግስት ወዶ ሳይሆን በግዱ ዴሞክራሲያዊ ይሆናል። አለበለዚያ ሕዝብ ውክልናውን ስለሚያነሳበት የስርዓቱ ሕልውና ያከትማል። ስለዚህ፣ ዋናው ነገር መንግስትን መቀየር ሳይሆን ሕዝብን መቀየር ነው። ቁም ነገሩ ያለው ሕዝብ መብትና ነፃነቱን አውቆ በራሱ እንዲያስከብር ማድረጉ ላይ ነው። ሕዝብ ስለ መብቱና ነፃነቱ ያለውን ግንዛቤ በመቀየርና ጠያቂ የሆነ ማህብረሰብ መፍጠር እስካልተቻለ ድረስ መንግስት መቀያየሩ “ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም” የሚሉት አይነት ነው።