ነሐሴ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ርዕሰ ዜና

የወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ወጣቶች በገፍ አፍሰው እያሰሩ ነው  የተመድ የሰብአዊ መብት ድርጅት በወያኔ የተደረገው ግድያን አስመልክቶ በአለም አቀፍ ደረጃ ምርመራና ማጣራት እንዲደረግ ሀሳብ አቀረበ  እነአቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ  በዛምቢያ ጠቅላላ ምርጫ ተደረገ  የአባይ ወንዝ ሞልቶ ካርቱም ከተማ ሊያጥለቀቅ እንደሚችል ተነገረ ዝርዝር ዜናዎች  በባህር ዳር እና በጎንደር ከተማ ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ የሆነ ወጣቶች ተይዘው በተለያዩ ቦታዎች የታስሩ መሆናቸው ታውቋል፡፤ እስር ቤቶቹ ጠበው ት/ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ተማሪዎችን ለማስሪያ እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ተገልጿል። ጳጳሱንና የሙስሊሙን መሪ በቴሊቪዥን ከማናገር ጀምሮ በህዝባዊ አመጹ ሽብር ላይ የወደቀው የወያኔ አገዛዝ በየቦታው የሃይማኖት አባቶችን አባገዳዎችን በማስተባበር የተቆጣውን ሕዝብ እንዲያረጋጉና አመጹን እንዲያስቆሙ ጥረት እያደረገ መሆኑ ይነገራል። በአንዳንድ ቦታዎ የሃይማኖት አባቶች የወያኔ መመሪያ አልቀበልም ብለው አቋማቸውን ከሕዝብ ጋር ያደረጉ ሲሆን በብዙ ቦታዎችም ሕዝቡ በተለይ ወጣቱ ከአመጹ እንቅስቃሴ ወደ ኋላ የማይል መሆኑን የነገራችው መሆኑ ታውቋል።  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኃላፊ ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ትናንት ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓም ጄኔቫ ላይ በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተደረጉ ግድያዎች ከመጠን ያለፉና አስከፊ መሆናቸውን ገልጸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርመራና ማጣራት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ኃላፊው ገለልተኛ የሆኑ የተመድ አጣሪዎች አገር ውስጥ ገብተው የማጣራቱን ስራ እንዲያከናውኑ የወያኔ አገዛዝ መፍቀድ ይኖርበታል ካሉ በኋላ ይህንን አስመልክቶ ከወያኔ ባለስልጣኖች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በሚገልጹ ዜጎች ላይ የጥይት ናዳ ማውረድ በጣም ያሳሰባቸው መሆኑን ገልጸው ግድያው ከጀመረ ጀመሮ ምንም ዓይነት ማጣራት ያልተድረገ መሆኑን አብራርተዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ደረሱት ግድያዎች እንዴት እንደሆኑ ለማወቅ የወያኔ አገዛዝ አጣሪዎችን እንዲያስገባ እጠይቃለሁ ማንኛውም በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ለማሰማት በመሰለፉ ብቻ የተያዘ ሰልፈኛ ባስቸኳይ መፈተታ አለበት ብለዋል። የወያኔ ቡድን ቃል አቀባይ የተመድ የሰብአዊ መብት ተቋም ያቀረበውን ሀሳብ እንደማይቀበል ገልጾ ማጣራቱን አገዛዙ ራሱ እንደሚያደረገው በመግለጽ ለማፌዝ ተቀናጧል።  በዛሬው ዕለት እነ አቶ በቀለ ገርባ በፌዴራል ፍርድ ቤት ቀርበው ስለቀረበባቸው ክሶች መልስ እንዲሰጡ ቢጠየቁ በሀገሪቱ የህግ የበላይነት እንደሌለ የቀረበባቸው ክስል አለአግባብ መሆኑንና ፍርድ ቤቱም ታዞ የሚሰራ እንጅ ነጻ አለመሆኑንም በመግለጽ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጸውዋል። ሁሉም ተከሳሾች የፍርድ ቤቱን ማንነት በማጋለጥና የክሱን መሰረተ ቢስ መሆን በማስረዳት መልስ ከመለሱ በኋላ ችሎቱ የተዘጋ መሆኑ ታውቋል።  በዛምቢያ ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2008 ዓም ለፕሬዚዳንት ቦታና ለምክር ቤት መቀመጫዎች ጠቅላላ ምርጫ ተድረጓል። በድምጹ አሰጣጥ ወቅት ላይ ምንም ዓይነት ግጭት ያልተከሰተ ሲሆን የምርጫው ውጤት በሚከሰትበት ወቅት ከፍተኛ ውጥረት ሊፈጠር እንደሚችል ባለስልጣኖች ይገምታሉ። ተወዳዳሪዎቹ አሸናፊ ሊሆኑ የሚችሉት የድምጹን አምሳ ከመቶ ካገኙ ብቻ መሆኑ ታውቋል። የመጀመሪያው ውጤት በሐሙስ ምሽት ላይ የሚታወቅ ሲሆን በ48 ሰአታት ውስጥ የምርጭ አስፈጻሚ አካሉ የምርጫውን ውጤት እንደሚያሳውቅ ተገልጿል። ቀደም ብሎ በተወዳዳሪዎች መካከል ውጥረት መፈጠሩናየተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ በመገደሉ ምክንያትም የምረጡኝ ቅስቀሳ ሂደት ለአስር ቀናት ያህል ተራዝሞ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።  በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 12 ሰዎች በኮሌራ በሽታ የሞቱ መሆናቸውን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቁ። የጤና ጥበቃ ሚንስትሯ ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ ከዋናዋ ከተማ ከባንጉ 300 ኪሎሜትር ላይ በምትገኘው በእንጁኩ ከተማ 19 በኮሌራ በሽታ የተለከፉ ሰዎች መታወቃችውና ከእነዚህ ውስጥ 8 ቱ ወዲያውኑ የሞቱ መሆናቸው ተነግሯል። ሌሎች አራት ሰዎች ዋናውን ከተማውን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች እንደሞቱ ተነግሯል። የኮሌራ በሽታ የሚስፋፋው በበሽታ በተለከፈ ምግብና ውሃ አማካይነት ሲሆን ተቅማጥና ትውከትን በማባባስ ሰውነትን አመንምኖ የሚገድል ነው፡፤ በአገራችንም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ አተት በሚባል የሚታወቀው ተመሳሳይ በሽታ በከፍተኛ ድረጃ መስፋፋቱና አሁንም በዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ በተደጋጋሚ ተዘግቧል።  በኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች ላይ በጣለው ተከታታይ ዝናም ምክንያት የአባይ ውሃ በመሙላቱ የካርቱም ከተማ በውሃ ልትጥለቀለቅ እንደምትችል የሱዳን መንግስት አስጠነቀቀ። የወንዙ ውሃ እየሞላ በመምጣቱ በአባይ ወንዝ ዳርቻ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለስልጣኖች ማስጠንቀቂያ የሰጡ ሲሆን በሁኔታው የምግብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችልም ተነግሯል። ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የሱዳን ግዛቶች በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 76 ሰዎች ህይወታችውን ያጡ መሆናችው ተገልጿል። ነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ርዕሰ ዜና  በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች እንደሚካሄዱ ተገለጸ  በጎንደር እና በባህር ዳር ውጥረቱ ቀጥሏል  የአውሮፓው ህብረት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ያሳሰበው መሆኑን በመግለጽ መግለጫ አወጣ  አማጽያን በማሊ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት አደረሱ  በደቡብ ሱዳን የእርስ በርሱ ግጭት እንደገና አገረሸ  ዛምብያ ውስጥ የሚካሄደው ምርጫ ውጥረት ተፈጥሯል ዝርዝር ዜናዎች  በሚቀጥለው ቅዳሜ ነሐሴ 7 ቀን በጎጃም ክፍለ ሀገር በዳንግላ፤ በኮሶበር፤ በቡሬ፤ በፍኖተሰላ፤ በደብረማርቆስ፤ በሞጣ፤ በቢቸና በደጀን፤ በደብረወርቅ በጉንዶወይን እንዲሁም እሁድ ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. በወሎ በመቂት፤ በላስታ ላሊበላ፤ በዋጎች ምድር፤ በሰቆጣ፤ በወልዲያ በራያ፤ በዋድላና ደላንታ፤ በደሴ፤ በኮምቦልቻ፤ በከሚሴ፤ በሸዋ ሮቢት ከፍተኛ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች እንደሚደረጉ ውስጥ ውስጡን ከሚተላለፉ በራሪ ማስታወቂያዎችና በሶሻል ሚዲያ አማካይነት ከሚተላለፉ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም እሁድ ነሐሴ 15 ቀን 2008 በአዲስ አበባ በሀዋሳ በአርባ ምንጭ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች እንደሚካሄዱ ተነግሯል።  ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ በሚል ብዛት ያለው ሰው ፍርድ ቤት አካባቢ ተገኝቶ የነበረ ሲሆን ሰውየው ባለመቅረባቸው ሕዝቡ ከወያኔ ወታደሮች ጋር ፍትጫ ውስጥ የገባ መሆኑ ይሰማል። አራዳ አካባቢ መንገዶች ተዘግተዋል። ጀምረው የነበሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጠዋል። ጎንደር ውጥረት ላይ ትገኛለች። በባህር ዳር ከተማ ሱቆች መስሪያ ቤቶች አሁን ዝግ ሲሆኑ የባንኮች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው ይባላል።  የአውሮፓው ማህበር ከብራስልስ ከተማ ባወጣው መግለጫ በቅርቡ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የተገደሉት ሰላማዊ የተቃውሞ ስልፈኞችና የጸጥታ ኃይል አባላት ያሳሰበው መሆኑን ገልጾ ጉዳት ለደረሰባችው የተሰማውን ሀዘን ይፋ አድርጓል። የአውሮፓው ህብረት በመገለጫው ሁሉም ወገኖች ከኃይል እርምጃዎች እንዲቆጠቡ ጠቁሞ ችግሮቹ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እንዲፈቱ አሳስቧል።  ሞፕቲ በተባለው በማዕከላዊ ማሊ ግዛት አማጽያን በአንድ ወታደራዊ ጦር ካምፕ ላይ ጥቃት ያደረሱ መሆናቸውን የማሊ ወታደራዊ ተቋም ቃል አቀባይ ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ ገልጿል። በጥቃቱ ምን ያህል ወታደሮች እንደሞቱና እንደቆሰሉ ባይገለጽም አምስት ወታደሮች የደረሱበት ያልታወቀ መሆኑ ተገልጿል።ጥቃቱን የፈጸመው ቀደም ብሎ ጥቃት ፈጽሞ ወታደሮችን አግቶ የነበረው አንሳር ዲን የተባለው ታጣቂ ኃይል ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ተሰጥቷል።  በደቡብ ሱዳን በመንግስት ኃይሎችና በሪክ ማቻር ደጋፊዎች መካከል ያለው ውጊያ እንደገና ያገረሸ መሆኑን ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ባለስልጣኖች የገለጹ መሆናቸው ታውቋል። ውጊያው የተጀመረው ከዋናው ከተማ ከጁባ ወደ ደቡብ ምስራቅ 150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የዩ በምትባለው ከተማ አካባቢ ሲሆን ወደ ዩጋንዳ የሚወስደው መንገድ በውጊያው ምክንያት ዝግ መሆኑ ተነግሯል። በሀምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በጁባ ከተማ በሳልቫኬርና በሪክ ማቻር ተከታዮች መካከል በተነሳ ግጭት 300 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውና ሪክ ማቻርም ከነተከታዮቻቸው ከተማውን ለቀው ወጥተው የሚመለሱት በጁባ ከተማ የሰላም አሰከባሪ ኃይል ሲሰማራ ብቻ መሆኑን መግለጻቸው የሚታወቅ ሲሆን ሳልቫኬር በምትካቸው ምክትላቸውን መሾማቸው ይታወሳል። በሌላ በኩል የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ከአካባቢው አገሮች የተውጣጣ ተጨማሪ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ወደ ደቡብ ሱዳን ለመላክ ያቀደውን ሀሳብ ደቡብ ሱዳን ውድቅ አድርጋዋለች ተብሏል። የተመድ ሀሳብ ተግባራዊ ከሆነ ሁላችንም ወደ ግኝ ግዛት እንቀየራለን በማለት የደቡብ ሱዳን ቃል አቀባይ ገልጿል። የደቡብ ሱዳን መንግስት የተመድን ሀሳብ ካልተቀበለ ድርጅቱ የመሳሪያ ማዕቀብን ጨምሮ የተለያዩ ማዕቀቦችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።  በዛምቢያ ነገ ሐሙስ ነሐሴ 5 ቀን በሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት የተፈጠረ መሆኑ ከአገሪቱ የሚወጡት ዜናዎች ይገልጻሉ። በስልጣን ከቆዩ አንድ ዓመት ተኩል ብቻ የሆናቸው የአሁኑ ፕሬዚዳንት በንግድ ስራ ላይ ከቆየቱና ተመክሮ አላቸው ከሚባሉት የናይትድ ፓርቲ ፎር ናሽናል ዴቨሎፕመንት ከሚባለው የተቃዋሚ ፓሪ መሪ ኃይለኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ዘንድሮ ለፕሬዚዳንትነት ምርጫ በሚካሄደው የምረጡኝ ቅስቅሳዎች በርክታ ግጭቶች የታዩባችው ሲሆን በአንድ ወቅትም የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ በጥይት ተመቶ በመገደሉ ቅሰሳው ለ 10 ቀናት ያህል ተቋርጦ እንደነበር ታውቋል። በምርጫው ወቅትም ተጨማሪ ግጭቶች ይኖራሉ ተብሎ ተፈርቷል። ማንኛውም ተወዳዳሪ ከድምጹ 50 ከመቶ በላይ ካላገኘ የሁለተኛ ዙር ምርጫ ይካሄዳል ተብሏል። ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ርዕሰ ዜናዎች  በባህር ዳር የወያኔ አግአዚ ያቆሰላቸው ተጨማሪ ሰዎች ሞቱ፤ በርካታ ወጣቶችም ታሰሩ  በሌሎች ቦታዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ናቸው  በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው መግለጫ ብዙዎችን አሳዘነ  በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ወደደቡብ ሱዳን ተጨማሪ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ለመላክ ሀሳብ ቀረበ  በዳርፉር ብሉናይል እና በኮርዶፋን አካባቢዎች ስላም ሊሰፍን ስለሚችልበት ሁኔታ የሱዳን መንግስትና ተቃዋሚዎች ተስማሙ ዝርዝር ዜናዎች  በወያኔ የአግአዚ ኃይሎች ቆስለው በባህር ዳር ሆስፒታል ውስጥ ሲታከሙ ከሚገኙ ወገኖች መካከል 5 ሰዎች ማረፋቸውን ከአካባቢው ከተገኘው ዜና ለማወቅ ተችሏል። ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን በባህር ዳር ጸጥታ ያለ ቢሆንም ውጥረቱ ያለ መሆኑ ይነገራል። የወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በመዘዋወር ወጣቶችን በብዛት እያሰሩ መሆናቸው ታውቋል። መስሪያ ቤቶች እስካሁን ዝግ ናቸው፤ የትራንስፖስርት አገልግሎትም ተቋርጧል። በዳንግላ ከተማ መስርያ ቤቶች ዝግ ሲሆኑ ነዋሪውም ባለፈው እሁድ በባህር ዳር በአግአዚ ጦር በተገደለው ወገኑ ሞት ቁጣ ለአመጽ እየተነሳሳ መሆኑ ይታያል። ከአርብ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በተለያዩ ከተሞች በወያኔ አግአዚ ጦር የተገደሉ ዜጎች ቁጥር 97 መድረሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሲገልጽ በአንዳንድ ክፍሎች ግምት ቁጥሩ እስከመቶ አምሳ መሆኑ እየተገለጸ ነው። በህክምና እየተረዱ የሚገኙ ቁስለኞች በጣም በርካታ በመሆናቸውና ጉዳቱ የጸናባችው ህይወታችው በሚያልፍበት ወቅት የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ግልጽ ነው።  በሌሎች ቦታዎችም የሚደረጉ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ናቸው። በጎንደር በደንቢያ፤ በሙሴ ባምብ በሰራቆና ሳንጃ አካባቢዎች የወያኔ የአስተዳድር መዋቅሮች ተነስተው ሕዝቡ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ይገኛል። ከጎንደር ሁመራ የሚወስደውን መንገድ ሕዝቡ በመዝጋቱ የወያኔ ጦር መንቀሳቀስ ያልቻለ መሆኑ ይነገራል። በባሌ ጊንዲሂር ውስጥ ሕዝቡ እስር ቤት ጥሶ ገብቶ እስረኞችን ማስፈታቱንና፤ በባሌ ራይቱ ባለፈው እሁድ አርሶ አደሮች ከወያኔ አግአዚ ጦር ጋር ገጥመው 7 ወታድሮች መገደላቸውን በሶሻል ሚዲያ ከቀረቡ ዜናዎች ማግኘት ተችሏል።  በጎንደር የወያኔው አጋዚ ጦር ነዋሪው ከመኖሪያ ቤቱ እንዳይወጣ በከባድ መሳሪያ በመጠቀም አጥሮ የከለከለ ሲሆን አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ከስፍራው ካገኘነው ዜና ለማወቅ ችለናል። ባለሱቆች/መደብሮች ሊነሳ የሚችለውን አመፅና የቃጠሎ አደጋ በመፍራት እቃወቻቸውን እያሸሹ ሲሆን፣ በዛ ያሉ የከተማው ነዋሪዎችም የታጠቁትን ለመቀላቀል ወደ በረሃ እየወጡ እንደሆነም ታውቋል። ረቡዕ ነሕሴ 4 ቀን ኮሎኔል ደመቀን ጎንደር በወያኔ ፍ/ቤት ፍርድ ቤት እንደሚቀርብና ከዚህም ጋር ተያይዞ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ከቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ የከተማው ነዋሪ ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ከቤቱ ወጥቶ መገብየት የማይችልበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች ህዝብ ከወያኔ ጋር እያካሄደ ያለው ውጊያ እንደቀጠለ ነው።  አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ሰሞኑን በተለያዩ ቦታዎች ስለተካሄዱት ሕዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቅሴዎች በሚመለከት አጭር መግለጫ አውጥቷል፡፡ መግለጫው በተለያዩ የአማራና የኦሮሚያ አካብቢዎች የተፈጠሩት ግጭቶች በጸጥታ ኃይሎችና በሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ በመድረሱ የአሜሪካ መንግስትን ያሳዘነ መሆኑን ገልጾ ሰልፎቹ ያልተፈቀዱ መሆናችውንም አውቀናል በማለት የተደረጉትን ስለፎች ለመውቀስ ሞክሯል። የአሜሪካ ኤምባሲ የወያኔ አግአዚ ወታደሮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰድዱትን አረመኔያዊ ተግባር ከማውገዝ ተቆጥቦ ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው ያካሄዱትን ሰልፍ ለመውቀስ ማዘንበሉ ብዙዎችን ከማስገርም አልፎ አሳዝኗል።  በደቡብ ሱዳን ጽጥታን ለማስከበር በተመድ ስር 4000 ተጨማሪ የአካባቢው ወታደሮች እንዲጨመሩ ሀሳብ የቀረበ መሆኑ ታውቋል፡፤ ተጨማሪው ኃይል የሚሰማራው በጁባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ይህ ኃይል ከተሰማራ ጸጥታውን ያረጋጋል ተብሎ ታምኖበታል። ኃይሉ በሱዳን ውስጥ ያለውን የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ቁጥር ወደ 17 ሺ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል። ይህን ተጨማሪ ጦር የደቡብ ሱዳን ባለስልጣኖች ካልተቀበሉ የመሳሪያ ማዕቀብ ውሳኔም እንደሚተላለፍ ተገልጿል። የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በተያያዘ ዜና የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ማምረቻ ተቋሞችን ለመገንባትና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማስፋፋት የደቡብ ሱዳን መንግስት ከቻይና መንግስት 1.9 ቢሊዮን ዶላር የጠየቀ መሆኑ ተገልጿል። የቻይና መንግስት ጥያቄውን ተቀብሎ ገንዘቡን የሚሰጥ ከሆነ ከሶስት ዓመት በፊት የተዘጋው ና በዩኒቲ ግዛት የሚገኘው የነዳጅ ማምረቻ ጣቢያ ታድሶ ስራውን እንደሚጀምር የተገለጸ ሲሆን በጁባ እና ዋው በሚባለው ከተማ መካከል ያለውን አውራ መንገድ ለመስራት 700 ሚሊዮን ዳላር ይመደባል ተብሏል። ይሁን እንጅ የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑን ሳይረጋግጥ የቻይና መንግስት ገንዘቡን እንደማይሰጥ ተገምቷል። በደቡብ ሱዳን የኢኮኖሚው ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ሰራተኞች በወቅቱ ደሞዝ የማይከፈላችው ከመሆኑም በላይ የዋጋ ንረቱም በ600 ከመቶ የጨመረ መሆኑ ይነገራል።  በዳርፉር፤ በብሉ ናይል እና በኮርዶፋን አካባቢዎች ሰላም ስለሚሰፍንበት ሁኔት በሱዳን መንግስትና በዋና ዋና አማጽያን ኃይሎች መካከል ነሐሴ 2 ቀን በተመድ አስታራቂነት አዲስ አበባ ላይ ስምምነት መደረጉ ተነገረ። ላለፉት ዓመታት በሶስቱም አካባቢዎች በተነሳው አመጽ ምክንያት በ10 ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ መሆናችው ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት ስምምነት የተደረገው በቅድሚያ ተኩስ አቁም አድርጎ ስላም ለማስፈንና የሰብአዊ እርዳታ ወደ ተጠቀሱት ቦታዎች ሊደርሱ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ በዘላቂው ሰላም ላይ ለመዳራድርና ለመፈራረም ነው። ነሐሴ 2 ቀን 2008 ዓም ርዕሰ ዜናዎች  በባህር ዳር በወያኔው የአግአዚ ጦር የተገደሉት ወገኖች ቁጥር 30 ሲደርስ ከ60 በላይ ቆስለዋል ተባለ  ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥለው ዋሉ  በማሊ የተመድ አስከባሪ ኃይል አባላት የፈንጅ አደጋ ደረሰባቸው  የሳኦ ቶሜ ፕሬዚዳንት ከምርጫ ውድድር ራሳቸውን አስወገዱ  ሙጋቤ ተቃዋሚዎችን አስጠነቀቁ  በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምስራቃዊ ክፍል የታጠቁ ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን ገደሉ ዝርዝር ዜናዎች  እሁድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ባህር ዳር ላይ በተደረገው የተቃውሞ ስልፍ የወያኔ አግአዚ ወታደሮች የገደሏቸው ዜጎች ቁጥር 30 መድረሱንና ከ60 በላይ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል። የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ። ለአንዳንዶቹ የቀብር ስነስርዓት የተደረገ ሲሆን ከደብረ ማርቆስ እና ከአዲስ ዘመን ለመጡት አስከሬኑን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ለመውስደ ዝግጅት ሲደረግ የቆየ መሆኑ ታውቋል። በዛሬ ቀን መስሪያ ቤቶች እና የስራ ተቋሞች ዝግ ሆነው ውለዋ። በተለያዩ ቦታዎች የተቃውሞ ሰልፎች ሲደረጉ መዋላችው ከአክባቢው የሚገኙ መረጃዎች የሚገልጹ ሲሆን ቀበሌ 7 ቀበሌ 11 ቀበሌ 13 እና ቀበሌ 14 የተቃውሞ ስልፎች ከተደረጉባቸው መካከል ናቸው። በለቀምት ወለጋ በኮፈሌ አርሲ በድሬደዋ፤ በጉራዋ ሀረርጌ፤ በሃረሚያ ሀረርጌ በጊንዲሂር ባሌ እና በሌሎች ቦታዎች. በዛሬ ቀን የተቃውሞ ስልፍ ቀጥሎ የዋለ መሆኑም አንዳንድ ምንጮች ይጠቁማሉ።  እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም. በሰሜን ምስራቅ ማሊ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ይጓዙበት የነበረው ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ በጠመደ ፈንጅ በመጎዳቱ አንድ ወታደር መሞቱና ሌሎች አራት መቁሰላቸው ተነገሯል። ከጥቂት ጊዜ በኋላም ኪዳል ከሚባለው ከተማ አቅራቢያ በተመሳሳይ ሁኔታ የተቀበረ ቦምብ ፈንድቶ በሌላ ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ ሲገለጽ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ታውቋል። ለደረሰው አደጋ ኃይላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ከአልቃይዳ ግንኙነት ያላቸው እስላማውያን የታጠቁ ኃይሎች እንደሆኑ ይጠረጠራሉ።  የሳኦ ቶሜና የፕሪንሲፕ ፕሬዚዳንት ማኑኤል ፒንቶ ደ ኮስታ እሁድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም፣ ከተድረገው ድጋሚው ምርጫ ራሳቸውን ያገለሉ መሆናቸው ተነገረ። በምእራብ አፍሪካ በምትገኘው ደሴት ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፕ ውስጥ ቀደም ብሎ በተካሄደው ምርጫ የአሁኑን ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ የድምጹን 50 ከመቶ ባለማግኘታቸው ለሁለተኛ ጊዜ ለውድድር እንዲቀርቡ መደረጉ ይታወሳል። በመጀመሪያ ዙር ምርጭ ፕሬዚዳንቱ 24.8 ከመቶ ሲያገኙ ተወዳዳሪያቸው 48.8 ከመቶ ማግኘታቸው ይታወቃል። ፕሬዚዳንቱ ምርጫው የተጭበረበረ ነው ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ራሳቸውን ከውድድር ያወጡት ቀድም የሚሸነፉ መሆናቸውን በማወቃቸው ነው ተብሏል። ብሎ የነበረው ምርጫ የተጭበረበረ ነበር በሚል ምክንያት ነው ተብሏል። ራሳቸውን ከምርጫው ካስወጡ ተወዳዳሪያቸው አሸናፊ እንደሚሆኑ የታወቀ ነው ተብሏል።  የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በጦርነት የወደቁ አርበኞችን ለማስታወስ ባደረጉት ንግግር የጸጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ስለወሰዱት ርምጃ አመስግነዋል። ተቃዋሚ ኃይሎች አገሪቱን ወደ ብጥብጥ እየወሰዷት ነው በማለት ወንጅለው የተቃውሞ ስልፎቹ ካልተገቱ ከፍተኛ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ዝተዋል። የታወቀው የዚምባብዌ የአርበኞች ማህበር ሰሞኑን በሙጋቤ ላይ ወቀሳ ሲያካሄድ የቆየ ሲሆን በስነስርዓቱ ላይ አባሎቹ ያልተገኙ መሆኑ ታውቋል።  በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምስራቃዊ ክፍል ኪቢሪዚ በሚባለው ከተማ የሚንቀሳቀሰው ዴሞክራቲፍ ፎርስ ፎር ዘ ሊበሬሽን ኦፍ ሩዋንዳ እየተባለ የሚጠራው የሩዋንዳ ሁቱ ታጣቂዎች ቡድን አባላት በአንድ ቀን ምሽት ሰባት ሰዎችን ገድለው የተሰወሩ መሆናቸው ከአካባቢው የተገኘው መረጃ ይገልጻል። ግድያው የተፈጸመው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በአካባቢው የአራት ቀን ጉብኝት አድርገው ከተመለሱ በኋላ ነው። ከ18 ዓመት በፊት የሁቱ ታጣቂዎች ከሩዋንዳ ተባረው ኮንጎ ከገቡ ጀምሮ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ፈጽመው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳችው ይታወሳል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s