በትናንትናው እለት August 26/2016 በጀርመን ሃገር በፍራንክፈርት ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

Reported by : Alemayehu Kidanewold

በጀርመን የኢትዮጵያን ስደተኞች ምክር ቤት እና በዲፒሀር ኢንተርቴይመንት አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ብዙ ህዝብ በተገኘበት በትናንትናው እለት August 26/2016 በጀርመን ሃገር በፍራንክፈርት ከተማ ተካሂዱዋል::

የተቃውሞ ሰልፉ ዋና አላማ የወያኔ ወሮ በላ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ በደሎች በአስቸኩዋይ እንዲያቆምና ለህዝቦች ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማስገደድ ብሎም በሃገር ቤት እየተደረገ ላለው ህዝባዊ እምቢተኝነት አጋርነትን ለመግለጽ ነበር::

በመላው ጀርመን የሚኖሩና ከሌሎች ሃገሮችም የመጡ ኢትዮጵያን የተሳተፉበት ይህ ትይንተ ህዝብ በነበረው የህዝብ ቁጥር ብዛት የተነሳ በታሪክም የመጀመርያው ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል::

ንጹሁን የኢትዮጲያን ባንዲራ ከፍ አድርጎ በማውለብለብና በከፍተኛ ስሜት እልህና ቁጭት እየተገደሉ ያሉትን ጀግናና ሰማእት ኢትዮጵያንን ፎቶዋቸውን በመያዝ ጥቁር በጥቁር ልብስ በመልበስ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይሄ አረመኔ አገዛዝ እያደረሰ ያለውን ፋሺስታዊ ጭካኔ ለአለም ህዝብ አሳይተዋል::

በሰላማዊ ሰልፍ ብሶቱን ለተናገረ ህዝብ ምላሹ በአጋዚ ጦር በጥይት መጨረስ የተያያዘውን ይህን ደም መጣጭ አውሬ በአስቸኩዋይ በቃህ ልንለው እንደሚገባ ተቃዋሚው በአንድ ድምጽ አሰምቶዋል::

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s