የአድዋ ድል 121ኛ አመት መታሰቢያና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ መደበኛ ስብሰባ በኑረንበርግ ከተማ

Reported by:- Alemayehu Kidanewold

Photo by:- Michael Mekonenne

ታሪክን በወርቅ ጽሁፍ ጽፈው ሃገርን በደማቸውና በአጥንታቸው ከፋይ አቁመው ለዚህ ትውልድ ባርነትን ሳይሆን ድልን፣ ውርደትን ሳይሆን ክብርን፣ ሃፍረትንና መሸማቀቅን ሳይሆን ሃገር ከአህጉር እና ከዓለም ከፍ እንድትል ያረገንን የአድዋ ድል ለ121ኛ ጊዜ ጀግኖች አባቶቻችንን በማስታወስ በድምቀት ተከብሮዋል::

ማርች 4/2017 ዓም ከቀኑ 2pm ላይ የተጀመረው ስብሰባ በአድዋ ድል ለተሰዉት ሰዎች እና በአሁኑ ሰአትም በወያኔ ነፍሰ ገዳይ ፋሽስት ቡድን በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች ለሃገራቸው ለሚሰዉ ጀግኖች ሰማእታት የ 1 ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ተጀምሮዋል:: በመቀጠልም የአድዋን ድል በተመለከተ አጠር ያለ ፊልም ለታዳሚው ለእይታ በቅቶዋል::

አቶ ልዑል ቀስቅስ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ዋና ሊቀመንበር ለድርጅቱ አባላት የእንኩዋን ደህና መጣችሁ ንግግር በማደረግ በአሁኑ ሰአት በሃገር ቤት በተለያዩ ክልሎች ከወያኔ ስርአት ጋር እየታገሉ የሚገኙትን ኢትዮጵያን በተለያየ የማህበራዊ ድህረ ገጾች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ፎቶዋቸውን በመለጠፍ ወያኔን በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ እያረገው ሲሆን እነዚህም የነጻነት ታጋዮች መረጃቸውና ፎቶዋቸው የማህበራዊ ድህረ ገጾች ወይም ዌብ ሳይት ላይ ከተለቀቁ በሁዋላ በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚሰወሩ ወይም እንደሚገደሉ በግልጽ እየታየ ነው:: ይህም ደግሞ ትግሉን እያኮላሸው በዙ ጀግኖች አርበኞችም እየተሰዉና ከባድ ዋጋን እያስከፈለም ይገኛል::ስለሆነም ማንም ሰው ይህንን መረጃ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የማውጣት ስራ በፍጥነት መቆም እንዳለበት ተናግረዋል::

ስብሰባውን አቶ ጥላሁን ጉደታ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ዋና ጸሃፊ፣ አቶ ቢክሰኝ ኌይለ ልዑል የድርጅቱ በባየር ምክትል ሊቀመንበር ፣ አቶ ዓለማየሁ ኪዳነወልድ የድርጅቱ በቩርዝቡርግና አካባቢው ዋና ሊቀመንበር፣ አቶ ሮዳስ ተስፋየ የድርጅቱ በሄሰን አካባቢ ፕሮፖጋንዳና ቅስቀሳ መርተውታል::

በስብሰባውም ላይ አቶ ጥላሁን ጉደታ የአባላትን የስራ ድርሻና ሃላፊነትን በአግባቡ መወጣት በሚል ርዕስ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን በንግግራቸውም በየክልልሉ የሚገኙት አንዳንድ የአመራር አባላት የተሰጣቸውን የስራ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ እንዳልሆነና በአባላቱና በከፍተኛ አመራሮች መሃል ክፍተት እየፈጠሩ መሆናቸው ተገልጾ ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል::

ድርጅቱ 15 የስልጣን ተዋረድ ወይም ቅደም ተከተል ያለው ሲሆን የስራ ድርሻቸውም በወረቀት ታትሞ ለሁሉም የአመራር አባላት እንደተሰጠ እና ያንንም በመመልከት ሰራችውን በጥንካሬ እንዲሰሩ አሳስበዋል::

በመጨረሻም ከአባላቱ ለተንሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የስብሰባው ፍጻሜ ሆንዋል::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s