‹‹ አውሬነት Vs ሰብዓዊነት ››

(መላኩ አላምረው)

ሁሉም የምድር ቁሳቁስ (ራሷን ምድርንም ጨምሮ) ለሰው ልጅ ተፈጠሩ እንጅ ሰው ለቁስ አልተፈጠረም፤ ለቁስም አይኖርም፡፡ በምድር ላይ ከሰው ልጅና ከሕይወቱ በላይ ክብር ልንሰጠውም ሆነ ጥበቃ ልናደርግለት የሚገባ ምንም ነገር መኖር የለበትም፡፡ በተለይም የሰውን ልጅ ክቡር ሕይወት ከቁሳቁስ ጋር ማነጻጸር… በተለይም ከሰው ልጅ ይልቅ ለቁስ ማድላት… ይህ የመጨረሻው የውርደት ጥግ ነው፡፡ ይህ በራስ ፈቃድ ከሰውነት ተራ ወጥቶ አውሬነትን መቀላቀል ነው፡፡ (፡›አውሬ ሆዱን የሚሞላለትን የሚበላ ነገር እስካገኘ ድረስ ስለ ነፍስ መጥፋት ጉዳዩ አይደለም፡፡ ያገኘውን ሁሉ እያረደ እየበላ ሕይወቱን ማስረዘም ላይ ብቻ ያተኩራል፡፡ የእርሱን ነፍስ ለማቆየት ሲል የሌላውን ነፍስ ያጠፋል፡፡ አውሬ የሌላው ነፍስ እንደርሱ ነፍስ ብቸኛ የመኖር ዋትና መሆኗን ይረሳል፡፡ በቃ ! ከራበው ማረድ ነው፡፡ እንዲያውም የሌሎችን ነፍስ በማጥፋት ደም ካላፈሰሰ የበላሁ አይመስለውም፡፡ ባጭሩ አውሬ የራሱን ነፍስ ለማኖር የሌላውን ነፍስ ያለ ርህራሄ የሚያጠፋ የምድራችን አረመኔና ጸረ-ሕይወት ፍጡር ነው፡፡)
የሰው ልጅ ግን እጅግ የሚያስተውል አዕምሮ የተሰጠውና ለፍጡራን ሁሉ የሚራራ ክር ፍጥረት ነው፡፡ በተለይም ለመሰሉ ለሰው ልጅ ሕይወት መኖር ዋጋ ይከፍላል፡፡ (ከአውሬዎች ለመጠበቅም አዕምሮውን ይጠቀማል፤ አንዱ ለአንዱ ጋሻ ይሆናል፡፡) ነገር ግን… ሰው በባሕርይው ተለዋዋጭ ፀባያት አሉትና… ሲያድለው ወደ መልአካዊነት ይለወጥና ሁሉንም እኩል ያፈቅራል፡፡ ለሁሉም እኩል ይራራል፡፡ ሳያድለው ወደ እንስሳዊነት ይወርድና ለሆዱ ብቻ የሚኖር ይሆናል፡፡ ከሰው ልጆች ይልቅ ሆዱን የሚሞሉ ቁሳቁሶችን አስበልጦ መውደድ ይጀምራል፡፡ በጣም ሲከፋም ወደ አውሬነት ተቀይሮ የገዛ ወንድም እህቶቹን አሳዳጅ ይሆናል፡፡ በራበው ሰዓት ያገኘውን ሁሉ ማረድ ይጀምራል፡፡ በዚህ ሰዓት የሰዎችን ምክር አይሰማም (አውሬ ሆኗላ)፡፡ እንስሶችንም ሆዱን ለመሙላት ብቻ ነው የሚፈልጋቸው፡፡ የእርሱ ሕብረት አብረውት ከሚገድሉ ጋር ብቻ ይሆናል፡፡
የሚያሳዝነው ደግሞ ወደ አውሬነት የተለወጠ ሰው ይህን ሁሉ ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ሲያከናውን አለማስተዋሉ ነው፡፡ የማስተዋል ጸጋውን ከሰውነት ወደ እንስሳነት በተቀየረ ጊዜ አጥቶታልና የሚያደርገው ነገር ሁሉ ልክ ይመስለዋል፡፡ መግደል የመኖር አንዱ መንገድ እንጅ ነውረኛ የአውሬ ፀባይ መሆኑ ፈጽሞ አይታየውም፡፡ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ወደ አውሬነት ፀባይ የገባን ሁሉ ቆም ብለን እናስብ፡፡ እየተናገርሁ ያለሁት ነገር ተረት ተረት አይደለም፡፡ የሰው ልጅ የሕይወት ሐቂቃ እንጅ፡፡ ከአውሬነታችን ካልተመለስን በቀር ሰብዓዊነትን ልንላበስ አንችልም፡፡ ሰብዓዊነትን ካልተላበስን ደግሞ ከሰዎች ጋር በሰዋ አኗኗር ለመኖር እንቸገራለን፡፡ የሰው ልጅ ብቸኛው የመሸናነፊያ መሳሪያ ‹‹ፍቅርና›› ነው፡፡ ፍቅር ካለ ይቅርታ አለ፡፡ ‹ፍቅርና ይቅርታ ደግሞ በአውሬ ልብ ውስጥ አያድሩም›፡፡
ለገንዘብና ገንዘብ ለሚገዛቸው ቁሳቁሶች ሲባል የሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት መረገጥ የለበትም፡፡ በተለይም በሕይወት የመኖር መብቱን ከፈጠረው ከአምላኩ በቀር ማንም ሊወስንለት አይገባም፡፡ አይደለም የሰው ልጅ ሕይወት የማንኛውም ሕይወት ያለው ፍጡር ነፍስ ከፈጣሪ የተሰጠች ምትክ የሌላት ውድ ሀብትና የመኖር ምስጢር ናት፡፡ ይህች የሕልውና መሠረት በፍጡራን ቁጥጥር ስር የምትሆንበት ተፈጠሯዊም ሆነ ሌላ ምንም ምክንያት የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ “ሰዎች” የሰዎችን ሕይወት የመስጠትም የማጥፋም መብቱ የላቸውም፡፡ ይህ አውሬነት ነው፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s